በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የቆየዉ የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ዛሬ በስኬት ተጠናቋል ።

በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የቆየዉ የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ዛሬ በስኬት ተጠናቋል ።

***

ሚቴዩ ፣ሐምሌ 5/2016

በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በሁለት የፈተና መስጫ ጣብያዎች ላለፉት ሦስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የ2016 የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና በዛሬዉ ዕለት በስኬት ተጠናቋል ።

በዚህ የመጀመሪያው ዙር 6,300 በላይ የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ ተማሪዎች በሙሉ ቅዳሜ ሐምሌ 6/2016 ወደ ቤተሰቦቻቸው የሚመለሱ ይሆናል ።

ተማሪዎቹ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ቤንች ሸኮ ፤ ምዕራብ ኦሞ እና ሸካ ዞኖች እንዲሁም ከጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ማጃንግ ዞን እና ከዲማ ወረዳ ውስጥ ከሚገኙ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደመጡ የሚታወቅ ነው ።

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሰላም ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ እየተመኘ ፈተናዉን በስኬት ለማጠናቀቅ አስተዋፅኦ ያደረጉትንም እያመሰገነ በቀጣይ ወደ ዩኒቨርስቲው የሚመጡትን የተጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በተመሳሳይ መልኩ ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጅቱን አጠናቋል።