በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ በሚዛን አማን ከተማ ውስጥ የሚሰራ የ4.4 ኪሎ ሜትር የመንገድ መብርት ዝርጋታ ፕሮጀክት አጀማመር ስነ-ስርዓት ተደረገ ፡፡ ሰኔ3/2013 ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ፡፡በከተማው ልዩ መጠሪያው ከሸኮ በር እስከ አማን ታፍ ነዳጅ ማደያ ድረስ ያለውን የ4.4 ኪሎ ሜትር የመንገድ መብራት ዝርጋታ ስራውን ፕላቲኒየም ኢንጅነሪንግ የተሰኘ ኮንትራክተር የተረከበ ሲሆን ፕሮጀክቱ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ነው፡፡ የስራውን መጀመር አስመልክተው ዶ/ር አህመድ ሙስጠፋ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕረዝዳንት ባስተላለፉት መልዕክት ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በዋናነት ከተቋቋመለት አበይት አላማዎች ማለትም መማር ማስተማር ፣ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ባሻገር አቅሙ በፈቀደለት ልክ በእቅድ ላይ ተመስርቶ እዲህ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች እንደሚያከናው ተናግረው የዛሬው የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት እና አንድነታችንን የሚያጠናክር ስራ መጀመር በመቻሉ እጅግ ደስታ እንደተሰማቸውና ስራው በተያዘለት ጊዜ ያላንዳች እንከን ጥራቱን ጠብቆ እንዲከናወን የቅርብ ክክትል እንደሚደረግ ተናግረዋል ፡፡ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በሶስቱም ግቢዎቹ በርካታ ለመማር ማስተማር ስራው ጉልህ አስተዋጽ ያላቸው ግዙፍ የግንባታ ፕሮጄክቶችን ሲያከናውን መቆየቱንና ይህም ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ስራውን ለማሳካት ወሳኝ መሆኑን ተናግረው በዛሬው እለት ደግሞ እንዲህ በማህበረሰቡ ውስጥ ፋይዳው ጉልህ የሆነ ስራ በተለይ የሚዛን አማን ከተማ ማህበረሰብ በምሽት ያለችግር መንቀሳቀስ የሚያስችለውን የመንገድ መብራት ዝርጋታ ስራ ፕሮጀክት ድጋፍ ማድረጉ እስከዛሬ ከነበረው በተሸለ ደረጃ ወደ ማህበረሰቡ የሚያቀራርበውና የሚያስተሳስረው በጎ ስራ መሆኑን የገለጹት ክቡር አቶ ፍቅሬ አማን የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ናቸው ፡፡አቶ ፍቅሬ አማን አያይዘውም መላው የሚዛን አማን ከተማ ማህበረሰብ የራሱ ሀብት ከሆነው ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በተለይም ከአመራሩ ጎን በመቆም መደገፍ ይገባዋልም ብለዋል ፡፡ የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ተመስገን ከበደ የፕሮጀክቱን ሰነድ ከአቶ ፍቅሬ አማን ተረክበው ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ለከተማዋ ነዋሪ ፋይዳው ጉልህ ከሆነው ፕሮጀከት መጀመርን አስመልክተው ደስታ የተሰማቸው መሆኑን ገልጸው በራሳቸውና በከተማው ማህበረሰብ ስም አመስግነዋል ፡፡ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በአረንጓዴ ልማት እና ከተማዋን በማስዋብ ስራም በጋራ ለመስራት ዝግጅት ላይ መሆኑን አቶ ተመስገን ከበደ አስታውሰው የዛሬው ፕሮጀክት መጀመሩን የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር በአረዓያነቱ በመልካም ጅማሮ ይመለከተዋልል ብለዋል ፡፡በተመሳሳይ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የዋናውን ግቢ ፌት ለፊት አጥር ተከትሎ የአንድ ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ ቴራዞ የማንጠፍ፣ አረንጓዴ ልማትና የማስዋብ ስራ ያስጀመረ ሲሆን ስራው ሲጠናቀቅ በዩኒቨርሲቲው ምቹና ማራኪ የትምህርት ስፍራ ከመፍጠር ባለፈ ለከተማው ውበት መሆኑም ታውቋል ፡፡በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው ቢዝነስ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተመስገን መኩሪያ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ሊያከናውናቸው በእቅድ ከያዛቸው ግዙፍና መካከለኛ ግንባታ ፕሮጀክቶች የዛሬው ከመካከለኞቹ አንዱ መሆኑን ተናግረው በቅርብ ጊዜያትም ሌሎች የዩኒቨርሲቲውንም ሆነ የአካባቢያችን ማህበረሰብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶች ስራዋች እንደሚጀመሩ አስረድተዋል ፡፡
Light of the Green Valley!
Mizan-Tepi University