በመማር ማስተማር፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት በተለይ ሰላማዊ መማር ማስተማሩን ስራ በማስቀጠል ረገድ አጋዥ በሆኑ ጉዳዮች ፣በተማሪዎች መሰረታዊ አገልግሎት በማተኮር ምልታ እያደረገ ሲሆን በመጀመሪያው ቀን ውሎው ከዩኒቨርሲቲውን ከፍተኛ አመራር እስከ ተማሪዎች ተወካዮች ድረስ ውይይት ያደረገ ሲሆን የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አህመድ ሙስጠፋ በተዘጋጀው ቼክ ሊስት መሰረት የተከናወኑ አበይት ተግባራትን በዝርዝር ለቡድኑ አቅርበዋል ፡ ፕሬዝዳንቱ ከተከናወኑ ተግባራት ባሻገር በሂደት ላይ የሚገኙ ስራዎችን ከማስታወሳቸውም ሌላ በቀጣይ ሁለት ሀገራዊ የሆኑ ወሳኝ የሆኑ ስራዎችን ለማከናወን ዩኒቨርሲቲው እያደረገ ስላለው ዝግጅት ሲገልጹ 6ኛው አገራዊ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ፣ዩኒቨርሲቲው የሚገኝበት አካባበቢ በደቡብ ምዕራ የአገራችን ክፍል እንደመኑ በአካባቢው ለሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች የዩኒቨርሲቲው ባለሙያዎች በሚፈለጉበት ቦታ እንዲሳተፉ በማድረግ ከአካባቢው መንግስት ጋር እየሰራ መሆኑን ፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶም በማህበረሰቡ ውስጥ ግንዛቤ የሚፈጥሩ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ፓናል ውይይቶችን ለማድረግ እቅድ እንዳለውም ተናግረዋል ፡፡
በዩኒቨርሲቲው አካባበቢም ሰላማዊ መማር ማስተማርን ስራ ለማስቀጠልና አስተማማኝ ለማድረግ ከአካባቢው ወጣቶች ጋር ዩኒቨርሲቲው በቅንጅት እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል ፡፡ በቀጣይም ቀናት የመጣው ቡድን በየደረጃው ከሚገኘው የዩኒቨርሲቲ አመራርና ሰራተኞች ጋር እንዳደረገው ሁሉ ከአካባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች በተለይም ከወጣቶች ጋርም የውይይት መድረክ እንደሚኖረውም ታውቋል ፡፡
Light of the green Valley!
Mizan-Tepi University