ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አዲስ 5 የቅድመ እና 2 የድህረ-ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞችን ሊጀምር መሆኑ ተገለጸ ፡፡የካቲት 1/2014 ዓ/ም ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ፡፡*********************************************************************************የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት እጩ ዶ/ር ካሳሁን ሙላቱ እንደተናገሩት የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በትላንትናው እለት ከተመለከታቸው አበይት አጀንዳዎች የተለያዩ የትምህር ፕሮግራሞችን ጥናት ላይ በመመስረት በገበያ ላይ ያላቸውን ተፈላጊነት በማጤን የቀረቡትን አዳዲስ የትምህርት ፕሮግራሞችን ለመክፈት በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ማስጸደቅ አንደኛው እንደሆነ አውስተው በዚህም መሰረት ሴኔቱ ያጸደቃቸው በቅድመ ምረቃ መርሀ-ግብር software Engineering, Bsc in Environmental Health, Veterinary science, Agri-business and value-chain Management, Environmental science የትምህርት መስኮች ነው። በድህረ ምረቃ መርሀግብር ደግሞ Msc in Environmental Health እና Msc in Botanical science የትምህርት መስኮች መሆናቸውን ገልጸዋል ፡፡ የፕሮግራሞቹ መከፈት ዩኒቨርሲቲው በቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የሚሰጣቸውን የትምህር መስኮች ከ47 ወደ 52 እንዲሁም በድህረ-ምረቃ ፕሮግራም ከ33 ወደ 35 ከፍ እንደሚያደርገውም ታውቋል፡፡ Mizan-Tepi University Light of the green Valley!