በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላና የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ኦርየንቴሽን መርሃግብር ተካሂዷል።
08/11/2016 ዓ/ም – ሚቴዩ
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በዛሬዉ እለት ”የምትተክል አገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አካል የሆነዉን የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላና የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና አሰጣጡ ዙሪያና ሊከተሉአቸዉ ስለሚገቡ መመሪያዎች ኦርየንቴሽን ተሰጥቷል።
በዋናዉ ግቢ በተካሄደዉ በመርሃ ግብር የተከበሩ አቶ ሀብታሙ ካፍትን የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቦርድ አባል ፤ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር ዋቆ ገዳና ምክትል ፕሬዚደንቶች ፤ ዶ/ር ደስታ ገነሜ የደ/ም/ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊ ፤ አቶ አገኘሁ ወርቁ የቤንች ሸኮ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ፤ የፈተና አስተባባሪዎች ፤ የፌደራል ፓሊስ አመራሮችና አባላት ፤ ተፈታኝ ተማሪዎችና የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ተሳታፊ ሆነዋል።
በተመሳሳይ መልኩ በቴፒ ካምፓስም ዋና ስራ አስፈፃሚዉ መንግስቱ ከተማ ፤ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደምሴ ደንቦ ፤ የሸካ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ በላቸው ጋራ ፤ ተማሪዎችና የካምፓሱ ማህበረሰብም ተሳታፊ ሆነዋል።
ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም እድል ከወዲሁ እንመኛለን።