በሁለት ዙር ሲሰጥ የቆየዉ ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ፍጹም ሰላማዊ በሆነና ከኩረጃ በጸዳ መልኩ ዛሬ መጠናቀቁ ተገለጸ።

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ዋቆ ገዳ በሁለት ዙር ሲሰጥ የቆየዉ ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ፍጹም ሰላማዊ በሆነና ከኩረጃ በጸዳ መልኩ ዛሬ መጠናቀቁን ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንቱ ፈተናዉ ከተቀመጠለት ሀገራዊ ተልእኮ አንጻር ግቡን እንዲመታ ርብርብ ላደረጉ አካላት የዩኒቨርሲቲው አመራር ፤ የጸጥታ አካላት ፤ የፈተና አስተባባሪዎች ፤ ችፎች ፤ ፈታኞች ፤ የመንግስት አካላት ፤ የዩኒቨርሲቲው ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ፤ የICT ባለሙያዎች ፤ ተፈታኝ ተማሪዎች ፤ የአካባቢዉ ማህበረሰብና እንዲሁም ሌሎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለተሳተፉ በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።