ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ የአማን ካምፓስን ጨምሮ 1,290 ተማሪዎችን በደማቅ ስነ ስርዓት ለ16ኛ ጊዜ አስመርቋል።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሚቴዩ ፣ሰኔ 27/2016
ዩኒቨርስቲው በዋናዉ ግቢ ከአራት ኮሌጆችና ከአንድ ትምህርት ቤት ቁጥራቸው 1,111 የቅድመ ምረቃ እንዲሁም በልዩ ልዩ የትምህርት መስኮች የተማሩ 179 የድህረ ምረቃ ፕሮግራም በድምሩ 1,290 ተማሪዎችን በዛሬው እለት አስመርቋል።



በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ክቡር አምባሳደር አል ቡሲራ ባስኑር በኢትዮጵያ ፤ ጅቡቲ ፤ እና የአፍሪካ ሕብረት የኢንዶኔዥያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ፤ የእለቱ ልዩ የክብር እንግዳ ፤ ክቡር አቶ ጸጋዬ ማሞ የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የመንግስት ዋና ተጠሪ ፤ ክቡር አቶ ሐብታሙ ካፍትን የቤንች ሸኮ ዞን አስዳዳሪና የዩኒቨርስቲው ቦርድ አባል ፤ ክቡር ዶክተር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፤ ክቡር አቶ ግሩም ተማም የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፤ ተጋባዥ እንግዶች ፤ የሃይማኖት አባቶችና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።