News
አለም አቀፍ የሴቶች ቀን (March 8) በዓል በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ተከበር"የሴቶችን የቁጠባ ባህል ማደግ ለህዳሴያችን መሠረት ነው" በሚል መሪ ቃል በአገር ዓቀፍ ደረጃ ለ41ኛ ጊዜ የተከበረው አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዩኒቨርሲቲያችንም በልዩልዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡
በዓሉ መላውን የዩኒቨርሲቲያችንን ማህበረሰብ ባሣተፈ መልኩ ሲከበር የበዓሉን መጀመር በፋይ ያበሰሩት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል፤ የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሲሆኑ ሴቶች ልዩ ድምቀታችንና ብርሃናችን ናቸው ያሉት ፕሬዝዳንቱ የሴቶችን በአመራር ዘርፍ ግንባር ቀደም ተሣተፊ እንዲሆኑ የሁላችንንም ርብርብ የሚጠይቅ በተለይም የሴት እህቶቻችንን ቁርጠኝነት ይጠይቃል ብለዋል፡፡ዶ/ር ፋሪስ ደሊል አሸናፊ ሴቶችን ሲሸልሙ
ይህም ይሣካ ዘንድ ልማታዊ መንግስታችን ልዩ ትከርት ሰጥቶ እየሰራ ነው ካሉ በኃላ አሁን አሁን እንደአገራችን ተጫባጭ ሁኔታ ብዙ የሚቀረን ቢሆንም የሴት ፓርላማ አባላት ቁጥር 38.9% መድርሱ በራሳ ጥሩ ማሣያ ነው ብለው ወደ በዩኒቨርሲቲያችንም በማተኮር በከፍተኛ አመራሩ እርከን ሴት እህቶቻችን ለማሣተፍ ትኩረት ሰጥተን መስራት ይገባናል ብለዋል፡፡የፓናል ውይይት ጽሁፍ በሴት መምህራን በቀረበበት ወቅት
በዓሉ በዩኒበርሲቲያችን ሴት መምህራን ለፓናል ውይይት የመወያያ ጽሁፍ በማዘጋጀት ውይይቱን የመሩት ሲሆን በተማሪዎች ድራማና ስነግጥም ቀርቧል፡፡በመጨረሽ ወንዶች ለሴቶች አጋርነታችውን የገለጹ በጽ በሁለቱም ፆታ የሩጫ ውድድር ተካሂዶ ለአሸናፊዎችም የቦንድ ሽልማት ተበርክቷል፡፡ በዓሉ ቴፒ ግቢም በደማቅ ስነ-ስርዓት በተከበረበት ወቅት ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያድረጉት አቶ ተማም ቃድሬ በምክትል ፕሬዘረዳንት ማዕረግ የቴፒ ግቢ ቺፍ ኤግዚኪቲቨ ኦፊሰር ናቸው፡፡ አቶ ተማም በመልዕክታቸው ሴቶች የአለማችን ግማሽ አካል እንደመሆናቸው ያለሴቶች ተሳትፎ የአገራችን ብሎም የዩኒቨርሲቲያችን ተልዕዕኮ ማሳካት የማይታሰብ ነው ብለዋል፡፡

Read more...Posted on 05/04/2017
የጥልቅ ተሀድሶ ውይይት መድረክ በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ

ከየካቲት 24 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የጥልቅ ተሀድሶ መድረክ በተሣካ ሁኔታ ተጠናቀቀ፡፡ በዩኒቨርሲቲያቸን ሁለቱም ግቢዎች በሚገኙ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲችንግ ሆስፒታል ሠራተኞች በቀረቡት የመወያያ ስነዶች እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ነባራዊ ሁኔታ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡

አቶ ወንድሙ ገብሬ ዬኒቨርሲቲው ቦርድ ሰብሳቢ


በውይይቱ የቤንች ማጂ ዞን ዋና አስተዳደሪና የዩኒቨርሲቲያችን አስተዳደር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ወንድሙ ገብሬ ውይይቱን የመሩ ሲሆን በሁለት ተከፍሎ በመምህራንና አስተዳደር ሠራተኞች በተካሄደው ውይይት እጅግ የተሟሟቀ ውይይትና የሂስ ግላሂስ መድረክ ሲሆን በዋናነት በኪራይ ሰብሳቢነትና አዝማሚያዎች ላይ ጥልቅ ውይይትና ግምገማ በማድረግ ተወያይቷል፡፡ አቶ ወንድሙ ገብሬ እንደተናገሩት በዩኒቨርሲቲው ተጨባጭ ሁኔታ የሚስተዋለውን ከፍተኛ የመምህራን ፍልሰት የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቦርድና ማኔጅመንቱ በቅንጅት ችግሩን ለመፍታት ጥረትን የሚያደርግ መሆኑን ገልጸው የመምህራንን መኖሪያ ቤቶች ችግር ቀስ በቀስ ለመፍታትም በሁለቱም ግቢዎች የመኖሪያ ቤት ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመር ገልጸዋል፡፡ የአካዳሚክ ዘርፍ ሠራተኞች ውይይት በከፊል (ሚዛን ግቢ)
የአካዳሚክ ዘርፍ ሠራተኞች ውይይት በከፊል (ቴፒ ግቢ) የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል በበኩላቸው ኪራይ ሰብሳቢነትን ለማክሰም በምናደርገው ትግል የመላው መምህራንና ሠራተኛ ጥረት ትግሉ የሚሻ በመሆኑ ሁላችን የበኩላችንን ማድረግ ይገባናል ብለዋል፡፡ ዶ/ር ፋሪስ ደሊል አያይዞውም የአስተዳደር ዘርፍ ሠራተኞች ውይይት በከፊል(ሚዛን ግቢ)
የአስተዳደር ዘርፍ ሠራተኞች ውይይት በከፊል(ቴፒ ግቢ)
በመምህራኖቻችንና ሠራተኞቻችም ችግር ተብለው የተጠቀሱትን የመልካም አስተዳደር እንከኖች ለመቀነስ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ሰራተኛውን ባሣተፈ መልኩ የተነሱ ነጥቦችን አንድ በአንድ ለይቶ በመያዝና በማቀድ ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት ይሰራል ብለዋል፡፡ የተሀድሶው መድረክ በነበረው የአንድ ሳምንት ቆይታው ከአመራሩ ጀምሮ እስከ ፈፃሚ ሠራተኛ ድረስ የሂስ ግለሂስ ግምገማ በማድረግ የተፈፀመ ሲሆን ተማሪዎችም ውይይት አድርገው በዩኒቨርሲቲያቸው የተሰተዋሉ አበይት ነባራዊ ችግሮች ላይ በጥልቀት ተወያይተዋል፡፡

Read more...Posted on 18/3/2017
Corruption the obstacle of our development

The 13th World anti-corruption day was celebrated in Mizan-Tepi University. On the occasion, His Excellency Tsegaye Mamo, acting president of the university lead the panel discussion and he underlined that corruption is the obstacle of our development that everybody hands up to fight against it. Moreover, the day was also celebrated colorfully at Mizan-Tepi University teaching hospital.

Read more...Posted on 28/12/2016
25ኛው የግንቦት 20 የብር ኢዮበልዩ በዓል

                      25ኛው የግንቦት 20 የብር ኢዮበልዩ  በዓል የግንቦት 20 ፍሬ በሆነው በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ

በሀገር አቀፍ ደረጃ "ብዝሃነትን ባከበረ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ህዳሴዋን በማፋጠን ላይ ያለች ሀገር ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል ለ25ኛ ጊዜ የተከበረው የግንቦት 20 የብር ኢዮበልዩ በዓል በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲም በተለያዩ ዝግጅቶች በሁለቱም ግቢዎቻችን ለአራት ተከታታይ ቀናት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፡፡

በዓሉ በፓናል ውይይት፤ በስፖርታዊ ውድድር፤ በሥነ-ጽሁፍ፤ በጭውውት፤ በድራማ እና በባህላዊ ሙዚቃ የተከበረ በመሆኑ በርካታዎችን አሳታፊ አድርጓል፡፡ ፓናል ውይይቱ በሶስት ዘርፍ ማለትም የዩኒቨርሲቲያችን መምህራንና አስተዳደር ሠራተኞች በአንደኛ ዙር፤ የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች በሁለተኛ ዙር እንዲሁም የዩኒቨርሲቲያችን ሴት ተማሪዎችና ሴት ሠራተኞች በሶስተኛ ዙር ተካሄዷል፡፡

ፓናል ውይይቶቹን በሚዛን ግቢ አቶ ፀጋዬ ማሞ፤ የዩኒቨርሲቲያችን የመ/ማ/ም/ማ/ል/ም/ፕሬዚዳንት የመሩት ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ አቶ ጀመረ ቆጭቶ፤ የዩኒቨርሲቲያችን ሀ/ቢ/ል/ም/ፕሬዚዳንት የቴፒ ግቢያችንን የውይይት መድረክ መርተዋል፡፡
                                                                       የፓናል ውይይት በከፊል

ዩኒቨርሲቲያችን በዓሉን ሲያከብር ከግንቦት 20 ፍሬዎች አንዱ በመሆኑና የሁሉም የሀገራችን ክፍል ማህበረሰብ በተገኘበት በመከበሩ እንዲሁም የሁሉም ማህበረሰብ ክፍል ተወካዩች ግንቦት 20 ካስገኛቸው ፍሬዎች ማለትም በትምህርት ተሳትፎ፤ በሴቶች ተሳትፎ፤ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ፍትሃዊ ስርጭት ወዘተ አስመልክቶ  ሁሉም በየዘርፉ የተወያዩበት በመሆኑ አከባበሩ የድል በዓሉ ትሩፋቶችን በመዘከር  ሰፊ ግንዛቤ የተፈጠረበት መሆኑ በውይይት ወቅት ተስተውሏል፡፡

በሌላ መልኩ በስፖርታዊ ዝግጅት የተከበረው ይህ የብር ኢዮበልዩ በዓል በሁለቱም ግቢዎቻችን መካካል ባለው ማህበረሰብ ዘንድ የወዳጅነትና የውድድር መንፈስ ከመፍጠሩም ባሻገር ለሌሎች ውድድሮችም ጠንካራ ተጨዋቾችን ለመለየት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ ተስተውሏል፡፡
በዓሉን አስመልክቶ በ2ቱም ግቢ መምህራንና አስ/ር ሠራተኞች መካከል የተደረገ የእግር ኳስ ውድድር
                                                የዞን ኪነት ቡድን በዕለቱ ባህላዊ ሙዚቃ ሲያቀርብ

ከዚሁ ጋር በተያይዞ ከግንቦት 15-18/2008 ዓ/ም የግንቦት 20 ድል በዓል 25ኛ ብር ኢዮቤልዩ በዓልን አስመልክቶ በትምህርት ሚኒስቴር ጋባዥነት አ/አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀው ኤግዝብሽን ላይ ዩኒቨርሲቲያችን በመማር ማስተማር፤ ምርምርና ማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ያከናወናቸውን ተግባራት በአውደ-ርዕዩ በማቅረብ ከፍተኛ አድናቆት ማግኘቱም ይታወቃል፡፡


Read more...Posted on 04/06/2016
የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ በአጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ውይይት አካሄደ፡፡

የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ከግንቦት 18-20/2008 ዓ.ም በሦስቱም የዩኒቨርሲቲው ግቢዎች ማለትም ሚዛን ዋናው ግቢ፣ ቲችንግ ሆስፒታልና ቴፒ ግቢዎች በመዘዋወር ከጎበኜ በኃላ ከዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች፣ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ጋር  በአጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ውይይት አካሄደ፡፡

በክቡር አቶ አድማሱ አንጎ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ማዕረግ የፍትህ ቢሮ ኃላፊና የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ስብሳቢ የተመራው የቦርዱ አባላት ቡድን ሀሙስ ግንቦት 18/2008 ዓ.ም  በቴፒ ግቢ እንዲሁም አርብ ግንቦት 19/2008 ዓ.ም  በሚዛን ግቢና ቲችንግ ሆስፒታል ተገኝተው  የተማሪዎች ማደሪያ ክፍሎችን፣ መማሪያ ክፍሎችን፣ ቤተ መጽሀፍትን፣  መመገቢያ አዳራሾችንና የምግብ አዘገጃጀት ሁኔታን፣ የቲችንግ ሆስፒታሉ ህክምና አሰጣጥ ሁኔታንና የህሙማን መኝታ ክፍሎችን እንዲሁም ቤተ-ሙከራዎችንና ትርትሜንት ፕላንቶችን  (treatment plants) ጨምሮ በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ ህንጻወችንና ዋና ቢሮችን ጎብኝተዋል፡፡
ከጉብኝቱ በኋላም የቦርዱ አባላት በቴፒና በሚዛን ግቢዎች ከሚገኙ ተማሪዎች፣ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ጋር አጠቃላይ በመማር-ማስተማር፣ ምርምርና ማህበረሰብ ድጋፍ እንዲሁም በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡ በምክክር መድረኩ የተሳተፉት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች፣ መምህራንና ሰራተኞች የቦርዱ አባላት በሁሉም ግቢዎች ተገኝተው የስራ እንቅስቃሴዎችን በማየታቸውና በማወያየታቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው በመግለጽ የዩኒቨርሲቲውን መልካም ስራዎችንና ተግዳሮቶችን ለቦርዱ አባላት በማቅረብ ሰፊ ውይይቶች ከተደረጉ በኋላ የቦርዱ አባላትም መልካም ስራዎች እንዴት መቀጠል እንዳለባቸውና ችግሮች እንዴት መፈታት እንዳለባቸው አቅጣጫ በማስቀመጥ የዩኒቨርሲቲው ማህበረስብ የዩኒቨርሲቲውን ራዕይና ተልዕኮ በቁርጠኝነት ለማሳካት መረባረብ እንዳለበት አስገንዝበው ቦርዱም በሁሉም መልኩ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቀዋል፡፡

ቅዳሜ ግንቦት 20/2008 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲውን አስተዳደር ቦርድ 30ኛ መደበኛ ስብሰባ በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት በማካሄድ ለዩኒቨርሲቲው ዕድገትና አጠቃላይ ሥራ መቃናት ጠቀሜታ ያላቸውን በርካታ ውሳነዎችን ወስነዋል፡፡


Read more...Posted on 01/06/2016
በሚዛን-ቴፒ ዪኒቨርስቲ በቴፒ ከተማ የታቀፉ ታዳጊ እግር ኳስ ተጫዋቾች

በሚዛን-ቴፒ ዪኒቨርስቲ በቴፒ ከተማ የታቀፉ ታዳጊ እግር ኳስ ተጫዋቾች
በርካታ ኮከብ እና ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ ቀጣይ ምንጫቸው ቴፒ እንደሚሆን አንጠራጠርም እነዚህን ታዳጊ ህፃናትን ፕሮጀክት በመንደፍ ተሰጦ ያላቸውን ልጆች በመመልመል፣ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በማሰልጠንና አስፈላጊውን ቁሳቁሶች በማቅረብ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርስቲ ሀገራዊ ግዴታውን እየተወጣ ይገኛል::

ዩኒቨርሲቲያችን በስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል 30 ምርጥ ታዳጊ ሕፃናትን እግር ኳስ በማስተማር ላይ ይገኛል። ከአምስት ዓመት በኋላ ምርጥ የወጣት ቡድን ይኖረናል። ሕፃናቱ በቀለም ትምህርታቸውም እንድጠነክሩ እየተመከሩ በዩኒቨርሲቲው እና በወላጆች ክትትልና ድጋፍ እየተደረገላቸው ያድጋሉ።

Read more...Posted on 27/05/2016

Message From President

Dear MTU academic staffs; administrative and technical support staffs; professionals in our teaching hospital; our students; our community and national and international partners, I am so happy and proud to be the member of MTU.
Read More ...

Faris Delil Yesuf (PhD) President